ዩኒቨርሲቲዎች በፈጠራ የታገዘ የሰውን ትኩረት ሊስብ የሚችል ስራ መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ

  • -

ዩኒቨርሲቲዎች በፈጠራ የታገዘ የሰውን ትኩረት ሊስብ የሚችል ስራ መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ

Print Friendly, PDF & Email

ደ/ማ/ዩ፡-የአማራ ክልል የዩኒቨርሲቲዎች የፀረ-ኤች አይቪ/ኤድስ ፎረም የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሔደ፡፡

አቶ ደሳለው ጌትነት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት ኤች አይቪ/ኤድስ በሀገር ደረጃ ወረርሽኝ በሚባል መልኩ ስርጭቱ የተስፋፋ በመሆኑ በተለይ ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጠቂ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በፎረሙ መልካም ተሞክሮዎች ማስፋትና የበሰለ ውይይት በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስትራቴጅ መንደፍ ይገባቸዋል፡፡

የፎረሙ ሰብሳቢ ሲ/ር ማርታ አስማረ ፎረሙ በግንቦት ወር 2009 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች ያሉባቸውን ችግሮች በመቀናጀት መፍታት እንዲችሉና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች/መስሪያቤቶች ጋር ያላቸውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር በማቀድ እንደሆነ ገልፀው የመድረኩ ዋና አላማም ዩኒቨርሲቲዎች ኤች አይቪ/ ኤድስን በመከላከል ረገድ ያከናወኗቸውን ተግባራ በመገምገም መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት ያለመ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በቀጣይም ፎረሙን የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በፎረሙ ላይ የተገኙት የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የኤች አይቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ የማስፋትና የማጠናከር የስራ ሂደት ባለሙያ የሆኑት አቶ ደስታ መራዊ የኤች አይቪ/ኤድስን ስጋት ለመቀነስ እያደረጉት ያለው ስራ በጣም አበረታችና ጥሩ ቢሆንም ማህበረሰቡ ትኩረት እየሰጠው ባለመሆኑ በፈጣራ የታገዘ የሰውን ትኩረት ሊስብ የሚችል ስራ መስራት እንደሚገባቸው በመናገር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮም ከፎረሙ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራትና ፎረሙን ለማጠናከር በርትቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በፎረሙ ሁሉም ነባር ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት ስድስት ወራት የኤች አይቪ/ኤድስን ስርጭት በዩኒቨርሲቲዎች ከመከላከልናከመቆጣጠር አኳያ የሰሯቸውን ተግባራት ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡ የፎረሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የደ/ማ/ዩ ያዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የፀረ-ኤች አይቪ/ ኤድስ ፎረም የተሳካ እንደነበር በመናገር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ወጣቶችን ሚያስተናግዱ በመሆኑ ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ከውይይቱ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች ወስደው በየዩኒቨርሲቲዎቻቸው በመተግበር ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .