Category Archives: News

  • -

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የግእዝ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍልን የማስተዋወቅ ዐውደ ጥናት ተካሄደ

 

ቋንቋና ስነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍልን ለማስተዋወቅ “የግእዝ ቋንቋና ሀገራዊ ፋይዳው” በሚል መሪ ሀሳብ  ከክልል ትምህርት ቢሮ ፣ ከዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት የውይይት ዓውደ ጥናት ተካሄደ ፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D1.jpg

በዚህ ዐውደ ጥናት ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካ/ጉ/ም/ ፕሬዚዳንት ይኽይስ አረጉ (ዶ/ር) እንደገለጹት ዛሬ የተገናኘነው ለዘመናት ተረስቶ ስለቆየው ሀገር በቀል ቋንቋ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ብሎም ወደ ቀደመ ክብርና ከፍታችን ወደ ማንነታችን ለመመለስ፣ የአባቶቻችንን እሴቶች ለመገንባትና ለመጠበቅ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡ ከዕውቀት፣ ከፍልስፍናና ከጥበብ ርስታችንም ጭምር ተነቅለን ቆይተናል፤ እኛም ትውልዱም ተጎድቶ ቆይቷል፤ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ማህበረሰቡንና ሕጻናትን መታደግ ከቻልን ከዚህ ሀገር በቀል ቋንቋ የምናተርፈው ዕውቀት ብዙ ነው ፡፡

የራሳችንን ቋንቋ ትተን በሌሎች ዓለማት ቋንቋዎች ስንማር፣ስንመራመር ቆይተናል፤ ነገር ግን ዛሬ በራሳችን ቋንቋ መማርና መመራመር መጀመራችን ወደ  ቀደመ ከፍታችንና ታሪካችን ለመመለስ አንዱ ማሳያ ነውና ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የግእዝ ቋንቋ ኪነ-ህንጻውን ስነ-ጽሁፍፉን፣ ስነ-መለኮቱን፣ ስነ-ቅመማውን ሲሰራ ከቆየ በኃላ በታሪክ አጋጣሚ ከቤተ መንግስት ወጦ በቤተ ክርስትያን ብቻ መቀመጥ ቻለ፤ በዚም ሁኔታ ስልጣኔያችን ተዳከመ። ሙሉ የሆነው ቋንቋ ጠፋ ኢትዮጵያ ራሷ ጠፍቷት ራሷን ለመፈለግ ዓለምን የምትዞር ሀገር ናት ።  በመሆኑም  አሁን ላይ የራሷን ቋንቋ በመፈለግ ላይ ትገኛለች በማለት ለተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የውይይቱን መክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D2.jpg

በዚህ የዐውደ ጥናት ላይ የግእዝ ቋንቋና ስነ ፅሑፍ ትምህርት ክፍልን አጀማመርና አጠቃላይ የግዕዝን  ምንነት በተመለከተ መወያያ ፅሑፍ ያቀረቡት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ተጠሪና መምህር መርጌታ አንሙት ዘመናይ እንዳሉት የግእዝ ቋንቋ ከ3 ሺ ዓመት በፊት ተግባራዊ የሆነ ቋንቋ ነበር። ብዙ ጊዜ መውደቅ መነሳት ያሳየ ቢሆንም ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ አሁን እስካለበት ጊዜ ድረስ 4 የውድቀት ደረጃዎችን ያሳየ ቋንቋ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ በአክሱም ዘመነ መንግስት ልሳነ ንጉስ ተብሎ ሀገራዊ ቋንቋ ሆኖ ሃይማኖታዊ እሴቶችን፣ ፖለቲካዊ፣ አሴቶች፣ ማህበራዊ የዳኝነት ስረዓቶች ሁሉም ተግባራት የሚካሄድበት ቋንቋ እንደነበር  አውስተዋል ። የግእዝ ቋንቋ ስለ ህክምና ፣ስለ ዳኝነት ስርዓት፣ስለ ዘመን አቆጣጠር፣ ስለ ስነ-ፈለክ ስነ- ምርምር  ስለ ስነ-ሰብ ወ.ዘ.ተ ዘመን ተሸጋሪ ስራዎች የተሰሩበት፣ ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን ለአለምም ጭምር የስልጣኔ በር የከፈተ፣ትውልድን በስነ-ምግባር የሚቀርፁና ሃገር ተረካቢ ትውልድ የሚያፈራ ታላቅ ቋንቋ እንደሆነ ገልፀዋል።

ከሌሎች ቋንቋዎች አንፃር ግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው የልዩ ባህሪይ ባለቤትም ነው፡፡ የግእዝ ቋንቋ ለመረሳቱ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ መነሻ የሚጠቀሱት የዮዲት ጉዲት ወደ ስልጣን መምጣት፣ እንዲሁም ነገስታት ከሌሎች  ክፍለ ዓለማት ካሉ መንግስታት ጋር ያደርጉት የነበረው የደብዳቤ ልውውጥ ግእዝን በመተው በአማረኛ ቋንቋ በመጠቀም እና የአማርኛ ቋንቋ  መስፋፋት በሌላ በኩል እንደ ላቶፕና መሰል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መስፋፋት እና ግእዝ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ተወስኖ መቀመጡ ተጠቃሽ ነጥቦች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D3.jpg

በባህዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን አንዷለም እና ዶ/ር አባ በአማን ግሩም #አባይን_በቅኔ እና #የፍልሰት_ምልሰት የተሰኙ ጥናታዊ ጽሑፎች በቅደም ተከተል ለውይይት ቀርበዋል። 

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D4.jpg

በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ከአቡነ ጎርጎሪዎስ ት/ቤት በመጡ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ከተጋባዥ የቋንቋው ሊቃውንት  ለታዳሚዎች ቅኔ የቀረበ ሲሆን በቀረቡ የጥናት ፅሑፎችና የመወያያ ነጥቦች ላይ ታዳሚዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፤ ምላሽና ማብራሪያም ከጥናት አቅራቢዎቹ  ተሰጦባቸዋል፡፡

This image has an empty alt attribute; its file name is %E1%8C%8D%E1%8B%95%E1%8B%9D5.jpg

በዐውደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የስረዓተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ሃላፊ አቶ ካሴ አባተ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የግእዝ ቋንቋን ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ተግባር አድንቀው በአማራ ክልልም አዲሱ ስረዓተ ትምህርት ተቀርፆ የግእዝ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት አካል አደርጎ ለመስጠት በአማራ ክልል በተመረጡ 4 ዞኖችና 6 ትምህርት ቤቶች ማለትም በደቡብ ጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በምስራቅ ጎጃም ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙከራ ደረጃ በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ይህን ተግባር በማጠናከር  ከሌሎች ዩኒቨርሲዎች ጋር በመሆን በተመረጡ ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችንና መምህራንን ማገዝና መርዳት ስረዓተ ትምህርቱ እንዲሻሻል ብርቱ ጥረት ማድረግ ለሀገሪቱም በሙያው የተማረ የሰው ሃይል ማፈራት  ከዩኒቨርሲቲው እንደሚጠበቅበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መርሃ ግብሩ በንግግር የዘጉት የዩኒቨርሲቲያችን አካ/ጉ/ም/ፕሬዚዳንት ዶ.ር ይኽይስ አረጉ እንደገጹት ለታሪካችን፣ ለቅርሳችን፣ ለማንነታችን ታላቅ ስለሆነው ግእዝ ቋንቋ በዚህ መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጦት መወያየት መጀመራችን በራሱ ለዚህች ሀገር ግእዝ ትንሳኤ ይሆናል ብለው እንደሚምኑ እና በዩኒቨርሲቲያችንም ቋንቋን ማበልፀግ እንደ አንድ የልህቀት ማዕከል አድርጎ እየሰራበት እንደሚገኝ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍልም በሌሎች ዓለማት ለሚኖሩ ዜጎች ሁሉ በድጅታል ቴክኖሎጂ ትምህርቱን ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም አድንቀው በመጨረሻም በዚህ ዐውደ ጥናት ላይ ተገኝታችሁ ለተሳተፋችሁ አካላት ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የግእዝ ቋንቋን ለማሳደግና ተተኪ ምሁራንን ለማፍራት በ2014 ዓ.ም ትምህርት ክፍሉን በመክፈት ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀምሪያ ድግሪ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡


  • -

በሶስት የግብርና ምርት ውጤቶች ላይ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደረግበትን አሰራርና የህግ ማዕቀፎች በሚመለከት ለባለድርሻ  አካላት ስልጠና ተሰጠ

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የግብርና ምርቶችና ተያያዥ  የምርምር ውጤቶች ላይ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚደርግበትን አሰራር በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት ህዳር 15/2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ የእምዕሮ ጥበቃ ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጧል።

የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ የደበረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው እንደገለፁት ጎጃም የሚታወቅባቸው የማር፣ የጤፍ እና የቅቤ ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማሰጠት ዩኒቨርስቲያችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ወደስራ የገባ መሆኑን ገልፀዋል። ጎጃም  የአምዕራዊ ንብረቶች ባለቤት ቢሆንም  በዚህ መስክ  የታሰበዉን ያህል ባለመሰራቱ  ብዛት ያላቸው በአእምዕሮ ጥበቃ ስር መሆን የሚገባቸው ዕዉቀቶች ባክነው ቀርተዋል።  እነዚህን እውቀቶች በማዳበርና በማሸሻል በአካባቢው በይበልጥ  በሶስቱ ምርቶች ትኩረት በማድረግ ወደ ስራ በመግባት ላይ ነን ብለዋል። አክለውም እንደገለፁት የሚመረቱ ምርቶች የንግድ ምልክት  (Trade Mark) እንዲኖራቸው ቢደረጉ አርሶ አደሮችን የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ ያነቃቃቸዋል፤ በመሆኑም ሁሉም የተጣለበትን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በማሳሰብ ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is patent2.jpg

የአእምሯዊ ንብረት ምንነትና  የሀገራችንን የሕግ ማዕቀፎች በሚል ርዕስ የአእምሯዊ ንብረት እሴት ልማት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርቁ  ስልጠና የሰጡ ሲሆን በስልጣናቸው ሶስት ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን እነሱም አእምሯዊ ንብረት ምንነት፣ አስተዳደርና የሕግ ማዕቀፎች ናቸዉ። የኢትዮጵያ የአእምሮ ጥበቃ ባለስልጣን ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የንግድ ምልክት ለማስመዝገብ  መከናወን ያለባቸው ተግባራት በመለየት ለንግድ ምልክት ፈላጊ አካላት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት ስለሆነ፤ የዛሬውም ስልጠና የጎጃም ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማሰጠት ተቋሙ ከሚሰራቸው  ስራዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ልዪ ጣዕም ጥራት ያላቸውና የግብርና ምርቶችን የገቢያ ተወዳዳሪነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት  ለማሳደግ የእእምሯዊ ንብረት ምርቶችን ከምርቶች በቀላሉ ለመለየት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል። በም/ስ/ጎጃም ዞን የሚመረቱ ምርቶችን የንግድ ምልክት ለማስመዝገብ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በተመለከተም አቶ ታደሰ ወርቁ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የሚመዘገበው ምርት በብዛትና በጥራት ለአካባቢው መለያ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በስልጠናው በተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም  ጠንከር ያሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። ከተነሱት ሀሳቦችም መካከል  የምርት ጥራት፣ ብዛት የገበያ ትስስር ፣ የህብረት ስራ አደረጃጀቶች ያላቸው ፉይዳ፣ የንግድ ምልክቱ ይዞት የሚመጣው ጥቅምች ላይ ሰፊ ወይይት ተደርጓል።

This image has an empty alt attribute; its file name is patent3.jpg

በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የፖተንት ምርመራ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ በኃይሉ መልከጼዴቅ ለምዝገባ የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎች የፓተንት ማመልከቻ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

በስልጠናው በቀረቡት ጽሁፎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለወደፊት በጋራ ለመስራት እንዲሁም የንግድ ምልክት ምዝገባው ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል።


  • -

The launch program of a project designed to adapt “Enset” for food in the Amhara region was held at Debremarkos University.

 

Debre Markos University: 24 September 2022 (Directorate of Public Relations and Communication) Debre Markos University and the Development Bank of Ethiopia jointly held a launch program for a project designed to adapt “Enset” for food in the Amhara region.

The President of  Debremarkos University Tafere Melaku (PhD) who gave the welcome speech at the program expressed his appreciation for the fact that the Development Bank of Ethiopia accepted the idea and decided to work with the Universiy with full intention of fulfilling social responsibilities.

This image has an empty alt attribute; its file name is pic2-1.jpg

He added that the project is a pioneer in the field and pointed out that even though “Enset” is a plant that has lived for a long time with us in our region, we do not use it except for baking bread, but it is a food security for more than twenty million people in the Southern part of our country.

He thanked the team of the project who made this project a reality by supporting the idea with research to ensure the food security of our community by bringing the experience of South Ethiopia region to Gojjam in Amara region. He has also promised to provide all the necessary support until the project is completed.

Finally, he conveyed his message that all of our university as well as the outside community should shoulder the responsibility of the project in a sincere spirit so that it can be completed in a better way as this project will be of great benefit to ensure food security for our zone specifically and for our region largely.

President of the Development Bank Ethiopia, Honorable Yohannes Ayalew (PhD) attended the project launch program to adapt “Enset” for food in the Amhara region and delivered a message.

This image has an empty alt attribute; its file name is pic3-1.jpg

In his message, the fact that the project is being launched at a time when the country is struggling to ensure food security makes its significance greater.  He added that when the project is completed, its role in protecting the ecosystem of the region is significant.

He also mentioned that the “Enset” plant is blessed with many good natural qualities and is preferred over other plants to ensure food security.

According to studies, “Enset” is the main source of food for more than 20 million citizens in Ethiopia.

Therefore, the purpose of this project is to enable farmers to produce more dried “Enset” or “Kocho” in the Amhara region to reduce drought and hunger by implementing this project to adapt it for food and to enable farmers to get more income by offering it to the market in addition to using it for food.

He stated that the Development Bank of Ethiopia encourages agricultural researches and innovative ideas related to the development of the country, especially food self-sufficiency.

A teacher and researcher from Wachamo University, Daniel Menor, presented his research paper titled ” ‘Enset’ Productivity and Adaptation”.

This image has an empty alt attribute; its file name is pic4-1.jpg

He explained in his article that “Enset” is a plant that can grow in both lowland and highland climates and has many benefits. Some of its uses include traditional medicine, industrial resources, food, and maintaining soil fertility.

He concluded his article by pointing out that the “Enset” plant has an irreplaceable role in ensuring food security as it can withstand climate change in different conditions and can remain without water for several times.

In this program, the concept of the project titled “Adapting ‘Enset’ for food in the Amhara region” was presented in detail by the project team.

This image has an empty alt attribute; its file name is pic5-1.jpg

As we understand from the article presented by Mr. Bawoke Tiruneh, a teacher and researcher of Debre Markos University and the proponent of this project, the project will be implemented in the next 10 years under the ownership of Debre Markos University. The Development Bank of Ethiopia on its own part has provided a financial support of 2 million birr for the project’s one-year implementation budget.

A discussion was held based on the two research papers presented, and various questions and important comments were given by the participating guests.

The President of Debremarkos University Tafere Melakun (PhD) and the President of Development Bank of Ethiopia Honorable Yohannes Ayaleu (PhD) made the concluding speech of the program.

In their speech, they both promised that they will work together to make the project grow into a comprehensive integrated project by providing professional and financial support.


  • -

እንሰትን በአማራ ክልል ለምግብነት ለማላመድ የተቀረፀ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ መስከረም 14/2015 ዓ.ም (የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር በአማራ ክልል እንሰትን ለምግብነት ለማላመድ የተቀረፀ ፕሮጀክት ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንትን ጨምሮ ከተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች፣ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንቶች እንዲሁም የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና መምህራን፣ ጥሪ የተደረገላቸው የዞንና የወረዳ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ ።

በዚህ መርሐ ግብር ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በሀገራችን ሀሳብን ፋይናንስ ማድረግ ባልተለመደበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግን ሃሳባችን ተቀብሎ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን በማለት በሙሉ ፍላጎት ከእኛ ጋር ለመስራት በመወሰናቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is pic2.jpg

አክለውም ፕሮጀክቱ በዘርፉ ፋና ወጊ እንደሆነ ገልፀው እንሰት በክልላችን አብሮን የኖረ ተክል ቢሆንም ከዳቦ ከመጋገሪያነት ውጭ ሳንጠቀምበት ኑረናል ፤ በአንፃራዊነት በደቡቡ የሀገራችን ክፍል ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን ህዝብ የምግብ ዋስትና እንደሆነ ጠቁመዋል። 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን ተሞክሮ ወደ አማራ ክልል ጎጃም በማምጣት እንሰትን (ቆጮን) ለምግብነት በማላመድ የማህበረሰባችንን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ አለብን በሚል ሃሳቡን በምርምር በማስደገፍ ወደ መሬት አውርደው ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ላደረጉት የፕሮጀክቱ አባላት ምስጋና አቅርበዋል። ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም ይህ ፕሮጀክት ለዞናችን ብሎም ለክልላችን ህዝብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ስለሆነ በተሻለ መንገድ እንዲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲያችንም ሆነ የውጪው ማህበረሰብ ፕሮጀክቱ የእኔ ነው በሚል የቅንነት መንፈስ ሃላፊነታቸውን በጋራ እንዲወጡም መልክታቸውን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ክቡር ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በዚህ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ፕሮጀክቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ደፋ ቀና በምትልበት ወቅት የተጀመረ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን አንስተዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የክልሉን ስነ-ምህዳር ከመጠበቅ አንፃርም የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሚሆን ገልፀዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is pic3.jpg

የእንሰት ተክል በርካታ መልካም የተፈጥሮ ባህርያትን የታደለ በመሆኑ ከሌሎች ተክሎች ይልቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተመራጭ እንደሆነም ጠቅሰዋል ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንሰት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ዋነኛ ምግብ ምንጭ ነው። በመሆኑም የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ በአማራ ክልል በተለይ ድርቅንና እርሃብን ለመቀነስ እንሰትን ለምግብነት የማላመድ ፕሮጀክት በመተግበር አርሶ አደሮች የደረቀ ቆጮን በብዛት እንዲያመርቱ እና ለምግብነት ከማዋል ጎን ለጎንም ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀገርን ለማልማትና በተለይም በምግብ ራስን ከማስቻል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግብርና ምርምሮች እና የፈጠራ ሀሳቦች እንደሚያበረታታ ገልፀዋል።

ከዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የመጡት መምህር እና በእንሰት ላይ መርምር ያደረጉት ተመራማሪ ዳንኤል መኖር “የእንሰት ምርታማነትና ማላመድ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፉ አቅርበዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is pic4.jpg

ባቀረቡት ፅሑፍ እንደገለጹት እንሰት በቆላማውም በደጋማውም የአየር ንብረት ክልል ውስጥ መብቀል የሚችል ተክል መሆኑንና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችም እንዳሉት አስረድተዋል። ከጠቀሜታዎቹም ውስጥ እንስት ለባህላዊ መድሀኒትነት፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት፣ ለምግብነት፣ ለቃጫ መስሪያነት፣ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ የሚሉት ጥቂቶቹ እንደሆኑ አብራርተዋል።  የእንሰት ተክል የአየር ንብረት ለዉጥን በተለያየ ሁኔታ በመቋቋም ያለዉሃ ለበርካታ ጊዜያት መቆየት በመቻሉ ከተመረተ በኋላ እስከ 7 አመት ሳይበላሽ መቆየት ስለሚችል  የምግብ ዋስትናን  ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለው በማስገንዘብ ፅሑፋቸውን አጠቃለዋል። “እንሰትን” በአማራ ክልል ለምግብነት ማላመድ በሚል ርዕስ የተቀረፀው ፕሮጀክ ንድፈ ሃሳብ  በዝርዝር ቀርቧል።

This image has an empty alt attribute; its file name is pic5.jpg

የፕሮጀክቱ ሀሳብ አፍላቂ መምህርና ተመራማሪ አቶ ባወቀ ጥሩነህ ካቀረቡት ፅሑፍ እንደተረዳነው ፕሮጀክቱ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ባለቤትነት በቀጣዮቹ 10 አመታት ውስጥ እንደሚተገበርና የኢትዮጵያ ልማት ባንክም የፕሮጀክቱን የአንድ አመት ትግበራ ማስጀመሪያ በጀት የ2 ሚሊዬን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ነው። በቀረቡት ሁለት ጥናታዊ ፅሑፎች ላይም ውይይት የተደረገ ሲሆን ጥያቄዎችና ጠቃሚ አስተያየቶችም ከተሳታፊ እንግዶች ተሰጥተዋል። 

የማጠቃሊያ ንግግር ያደረጉት የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ታፈረ መላኩን (ዶ/ር) እና  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ክቡር ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ሲሆኑ በንግግራቸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሮጀክቱን  ሙያዊና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ወደ ሁለገብ የተቀናጀ ፕሮጀክትነት እንዲያድግ ለማድረግ በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።


Search DMU

Upcoming Events

There are no upcoming events.

Partners

DMU Radio Broadcasting . . .